የኦሆዴድ/ኢህአዴግ መሪዎች ህዝቡ በፍላጎቱ
እንደማይመርጣቸው በሚገባ ስለተረዱ የተካሄደውን ምርጫ አጭበርብረው ስልጣን ላይ ለመቀጠል በማሰብ በምርጫው እለት ህዝቡን በታጠቁ
የሰራዊት አባላት አስከብበውት መዋላቸውን የገለፀው መረጃው ለተፈፀመው አስፀያፊ ተግባር የተቃወሙት የፖሊስ አባላትም እንዲታሰሩ
መደረጉን ታውቋል።
መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው የከተማዋ የፖሊስ ኮማንደር በኛ ላይ ሌሎች የሰራዊት
አባላት ጨምራችሁ ህዝቡን መበተን ትክክል አይደለም ከአቅማችን በላይ ነው አላልናችሁም ብሎ በተቃወመበት ጊዜ ሌሎች የፖሊስ አባላትም
ሃሳቡን መደገፋቸውና ሁኔታውን በጥብቅ ከተቃወሙት የፖሊስ አባላት መካከል ብርሃኑ የተባለ የፖሊስ አባል መታሰሩን የተገኘው መረጃ
አክሎ አስረድቷል።