Sunday, May 31, 2015

በአማራ ክልል ፍኖተ ሰላም ከተማ ውስጥ የተቃዋሚ ድርጅቶች የምረጡን የቅስቀሳ ፖስተሮች እንዳይለጠፍ በኢህአዴግ ስርዓት ካድሬዎች መከልከሉ ታወቀ።



በፍኖተ ሰላም ከተማ የሚገኙ ተቃዋሚ ድርጅቶች የምረጡን ቅስቀሳ የሚያመለክቱ ፖስተሮች እንዳይለጥፍ ግንቦት 13/2007 ዓ/ም ተከልክለው መዋላቸውንና ህዝቡ በበኩሉም የፈፀማችሁት ተግባር ትክክል አይደለም በማለት የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዱን የገለፀው መረጃው የስርዓቱ ታጣቂዎች ህዝቡን ለመበተን በወሰዱት ህገ ወጥ እርምጃም ብዛት ያላቸው ነዋሪዎች ጉዳት እንደደረሳቸው ለማወቅ ተችሏል።
   ጉዳት ከደረሰባቸው ዜጎቻችን ውስጥ ስማቸውን ለመግለፅ ያህል- ሙሳ አህመድ የተባለው ብር ሸለቆ እርሻ ልማት የሚሰራ፤ አሳምነው ቆዩና ሌሎች ስማቸው ያልተገለፁ እንደሆኑና እነዚህ ወገኖችም ክፉኛ ተደብድበው በህክምና ውስጥ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን፤ በዚህ ተግባር የተቆጣው ህዝብም ከዚህ በላይ ምን ይመጣብናል ብሎ በመቃወም ወደ አደባባይ መውጣቱን ተከትሎ የከተማው አስተዳዳሪ ሁኔታውን ለማረጋጋት ሲል በንፁሃን ወገኖች ላይ ጉዳት ያደረሱ ታጣቂዎችን እርምጃ እንወስድባቸዋለን ብሎ ለማረጋጋት መሞከሩን የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።