በኣካባቢው የሚገኙ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ እንዳመለከተው በኣማራና ቅማንት
ብሔረሰዎች መካክል የስርኣቱ መጥፎ ኣስተዳደር የፈጠረው ኣመታት ያስቆጠረ ግጭት የነበረ ሲሆን። የሚመለከተው የመንግስት ኣካል ሃላፍነት
ወስዶ መፍትሄ ሊያድርግበት ባለመቻሉ በየግዜው ግጭጡ እየተጠናከረ የዜጎቻችን ሂወት እያጠፋ እንደሚገኝ ታዉቀዋል።
በየግዜው እየተነሳ በሚገኝ ግጭት የኣካባቢው ነዋሪዎች ሰላማዊ ንሮ ለመምራት
እንዳልቻሉና በሕዳር 30/ 2008 ዓ.ም በተከሰተው ግጭትም ኣቶ ቻላቸው ንጉሴና ቸኮል ዋሴ የተባሉ ከብሔረ ቅማንት፣ ኣቶ ዋለልኝ
ምስክር ከኣማራ ብሔረሰብ በግጭቱ ምክንያት መሞታቸው ታዉቀዋል።
የኢህኣዴግ ገዢ ስርኣት የብሔር ብሔረስዎች ህዝቦች በኣል እያለ በሚልዮኖች
የሚገመት የህዝባችን ሃብት ወጪ በማድረግ በየኣመቱ ሕዳር 29 የሚያክብረው ለፖለቲካ ፍጆታ እንጂ ከልብ የመነጨ ሃሳብ ባለመሆኑ
ብቢሔረሰዎች መካከል ግጭቶች ሲያበረታ እንጂ መፍትሄ እያመጣ እንደማይገኝ የፖለቲካ ሙሁራን ገለፁ።