Saturday, December 19, 2015

በአምቦና በጅማ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች በኦሮሚያ ክልል ተነስቶ ያለው የኢህአዴግ ሰረአትን መጥፎ አካሄድ የመቃውሞ አላማ ያደረገ ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉ ተገለፀ።


     ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ እንደሚያመለክተው። በአምቦና በጅማ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ህዳር 29/2008 ዓ/ም ሰላማዊ ሰልፋ እንዳካሄዱ ከገለፀ በኃላ። ሰልፈኞቹ እጃቸውን ወደ ኃላ በማደረግ ታስረን ነው ያለን! በማለት መሬታችን ተወረረ።!  የኢህአዴግ አመራር  መሬታችንን ነጥቀው በመውስድ እነሱ ለሚወዱት እየጠቀሙ ነው።! ሌሎችም የሚሉ የተቃውሞ መፎክሮች  በመያዝ በአደባባይ በመወጣት ደምፃቸውን በጩኽት እንዳሰሙ ለማወቅ ተችሏል።
   በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ አባገነኑ ሰረአት በተለመደው ተግባሩ በህዝብ ላይ የመጨፍጭፍ እርምጃ በመውሰድ ከተለያዩ ቦታ የሰበሰባቸውን በርካታ የፊዴራል ፓሊሶች በማሰማራት መብታቸውን በመጠየቅ ላይ በነበሩ ወገኖች  በመሳሪያ ሃይል ለመበተን በወሰደው እርምጃ የተነሳ በርከት ያሉ ሰልፈኞች ለሞትና ለመቁሰል እንደዳረጋቸው የደረስን መረጃ ጨምሮ አመልክቷል።