Wednesday, December 16, 2015

በኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት ወስጥ 7 አመት ላገለገሉ ወተሃደሮች የማሰናበት ተግባር ከህግ ውጭ እየተሰራ ሰለሆነ ተቃውሞ ማነሳቱ ተገለፀ።



በገዥው የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ከ7 አመት በላይ ያገለገሉ ወተሃደሮች በጥያቄያቸው መሰረት ሊሰናበቱ እንደሚችሉ የሚፈቅድ  ህገ ደምብ  መኖሩን የገለፀው መረጃው።
   ቢሆንም ከ7 ኣመት በላይ አገልግለው ጥያቄ ያቀረቡ ወተሃደሮች ቅኑ ምላሽ የሚሰጥ አካል ስለማያገኙ በየቀኑ በቡዱን በመሆን  እግራቸው ወደ መራቸው በመጥፋት ላይ ሰለሚገኙ  ጋንታዎች በስው ሃይል እየተመናመኑ በመሄዳቸው የሰጉ ኣዛዦች ከሃይል 15 ግልጋሎታቸው የጨረሱ ወተሃደሮች ማሰናበት  በጀመሩበት ወቅትም ኣስራሩ በኮታ መሆን የለበትም በሚል በሰራዊቱ ውስጥ ተቃውሞ መነሳቱ ታወቀ።
   መረጃው ጨምሮ እንዳሰረዳው ሰራዊቱ ከሚያሰማቸው  የተቃውሞ ነጥቦች መካከል እነዚህ በኮታው መሰረት ህጋዊ ስንብታ እየተሰጣቸው ነው የሚባሉት ወታደሮች ግልጋሎታቸው ጨርስው ሳይሆን በወታደር ለመቀጠል ኣካላዊ ብቃትና  ጤንነት የሌላቸው  ናቸው እንጂ ጥያቄ ያቀረቡ ኣይደሉም በሚል  ተቃውሞውን በበለጠ  እንዳባባሱት ለማወቅ ተችለዋል።