በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን በድምፂ
ወያኔ ትግራይ የተሰናዳው ጥራት የሚል የግምገማ ስብሰባ ህዝቡ ባቀረበባቸው ሰፊ ጥያቄዎች መካከል ሙስና የሚመለከት እንደሆነ
ከተገለፀ በኃላ በዚህም የተነሳ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የገዢው ስርአት ሽሞኞች ስልጣናቸው ተገን በማድረግ በሚቀበሉት ጉቦ
ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ሃብት በማካበት የተለያዩ ድርጅቶች ሰርተው እየኖሩ ነው ሲል ህዝቡ በስብሰባው እንደገመገመ ለማወቅ
ተችሏል።
በስብሰባው ከሙስና ጋር በተያያዘ ከተገመገሙት የስርአቱ ሽሞኞች
መካከል ረዳት ኢንስፔክተር ክሊንተን ደሞዝ 2,400 ብር የወር ዶሞዙ እያለ 6 ሞቶ ሺ ብር የሚገመቱ ቤቶች እንደሰራ፤ ዋና
ሳጅን ዓንዶም የተባለው በሞቶ ሺ የሚቆጠሩ ቤቶች በዓዲ ረመፅና በሁመራ ከተማ እንደሰራ፤ አንጋው የተባለው የዞኑ የትራንስፖርት
ሃላፊ ከ5 ሞቶ ሺ ብር በላይ የሚገመት ድርጅት በሁመራ ከተማ ያለው ሲሆን በአጠቃላይ በምእራባዊ ዞን የከፋ የሙስና ተግባር
እንደሚፈፀም በማመልከት ህዝቡ አስቸኳይ መፍትሄ ይደረግልን ብሎ እንደገመገመ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።