ከታሕሳስ 4/16/2005 ዓ/ም በተካሄደው ስብሰባ የተገኙት የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ከቡሬ ከተማ ፤
ከፍኖተ ሰላም ፤ ከሰከላና ወንበርማ ወረዳዎች የተሰባሰቡ ሲሆን በስብሰባው የቀረቡ አጀንዳዎች መልካም አስተዳደር እናስፈን ፤ ነጋዴው ፈጣን እድገት እንዲያስመዘግብ መደረግ
ያለበት ጥረት በተመለከተ ሲሆን አጀንዳዎቹ ተቀባይነት አላገኙም ተሰብሳቢዎቹ
በማስከተል ቅድሚያ እንዲፈቱላቸው የሚፈሉጓቸውን ችግሮችን አቅርበዋል።
በደረሰን ዘገባ መሰረት የኢህአደግ ስርዓት እውቀታቸውንና ገንዘባቸውን በአገር ልማት በማዋል እራሳቸውን
፤ ወገናቸውንና አገራቸውን ለመጥቀም የሚንቀሳቀሱ ዜጎችን ህግና ደምብ በሚፈቅደው መሰረት አታስተናግዱም ቅድሚያ እምትጠይቁት ጉቦን
ነው ፥ የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች በስብሰባው በመነሳታቸው ስብሰባውን ሲመራ የነበረ ካድሬ በሁኔታው ተደናግጦ ከዓቅሜ በላይ ነው ሲል
እንደገለጸላቸው ለማወቅ ተችለአል።
በስብሰባው ጥያቄ ካቀረቡ ነጋዴዎች መካከል አቶ ተሻለ ፤ አቶ ካሴና አቶ መሓሪ የተባሉ ይገኙባቸዋል፣ በወር 150 ብር ገቢ የሌለው ነጋዴ እንዴት በዓመት 150,000 ብር ግብር
እንዲከፍል ይጠየቃል መንግስት የለም ወይ ? ሲሉም ጠይቀዋል።
ስብሰባውን እንዲመራ የተላከው ካድሬ የቀረቡትን ጥያቄዎች ከአቅሜ በላይ ስለሆኑ ምላሽ ለመስጠት ከክልል
የሚመጣ ሰው መኖሩን ለተሰብሳቢዎች ከገለጸላቸው በሁዋላ በስብሰባው ከተገኙት 400 ነጋዴዎች መካከል ከ 30 በስተቀር የተረፉት
ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።