Monday, December 10, 2012

በአላማጣ ወረዳ ፤በዋጃና ኩኩፍቱ አከባቢ ኗሪ የሆኑ በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች በወረዳዋ የደህንነት ሃላፊዎችና አባላት እየተዋከቡ መሆኑ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት ህዳር 20,2005 ዓ/ም የቀበሌዋ ኗሪዎች ተሰባስበው ፈጣሪያቸውን በማመስገን ላይ በነበሩበት ጊዜ የወረዳዋ የደህንነት አባላት ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመተባበር የአሸባሪዎች መዝሙር ስታስተጋቡ ተገኝታችሃል በሚል ሰበብ በርካታ ንጹሃን የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ማሰራቸውን ቷውቋል፣
በእምነታቸው ምክንያት ብቻ በአላማጣ ከተማ በሚገኘው እስር ቤት በእስር ላይ የሚገኙ ሞስሊም ወገኖቻችን መካከል፣
1-መምህር ሓብብ ዴረሳ
2-መምህር እድሪስ ለገሰ
3-መምህር ከድር አደም
4-አቶ ዓብደል ዓዚዝ መሓመድ ስራጅ
5-አቶ ሙራድ መሓመድ ያሲን
6-አቶ መብራህቱ ኢብራሂም
7-አቶ መስዑድ ቡግሳ ተፈሪ
8-ዓብዱ ድሬሳ በሚል ቅጽል ስም የሚታወቅ አንድ ዜጋ
9-አቶ አሚር ሸኽ አህመድ
10-ሽክ ስራጅ ኩቢ ዓሊ
11-ሸክ ዓብዱ መናን……….ይገኙበታል፣
እነዚህ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ጸሎት ለማድረግ ውሃ እንዳይሰጣቸው የተከለከለ ሲሆን በተጨማሪም በጭንቅላታቸው የነበረውን ጥምጣም በጸጥታ ሃይሎች መነጠቃቸውን ለማወቅ ተችለዋል፣
ይህ በእንዲህ እያለ የአከባቢው ሞስሊም ማህበረሰብ በላያችን ላይ እንዲህ ያለ ግፍ ሲፈጸም ዝም ብለን መቀመጥ የለብንም ለሃይማኖታችን መሰየፍ አለብን ሲሉ መደመጣቸውን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣
ንጹሃን ዜጎችን በመወንጀል ማሰርና በሃሰት ክስ ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብን ስራየ ብሎ የያዘው የኢህአደግ ስርዓት በወረዳዋ በእስር ላይ የሚገኙትን ሞስሊም ወገኖቻችንንም በተመሳሳይ መልኩ በአሸባሪነት ክስ በያዝነው ወር ወደ ፍርድ ለማቅረብ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ቷውቋል፣