Sunday, January 27, 2013

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ቁጥራቸው ከአንድ ሺ (1000) በላይ የሚሆኑ ሙስሊም ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እንደወጡ ቷውቋል፣



በዩኒቨርሲቲው ስር በሚገኙ ፔዳ ፤ ፖሊ፤ ይባብና ዘንዘሊማ ካምፓሶች ተመድበው በመደበኛ የትምህርት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ከነበሩት ከ1ኛ-4ኛ ዓመት ተማሪዎች የሚገኙባቸው 95% የእስልምና እምነት ተከታዮች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ መስገድ ተከልክለናል በሚል ዩኒቨርሲቲውን ለቀው ከወጡ ብሁዋላ የተወሰኑት ወደየ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰው የሄዱ ሲሆን ቀሪዎችም የጉዞ ትኬት ቆርጠው ለመሄድ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
ተማሪዎቹ የኒቨርሲቲውን ለቀው ለመሄድ የተገደዱበት ዋና ምክንያት ከሦስት ሳምንታት በፊት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ሞስሊም ተማሪዎች በግቢው ውስጥ እንዳይሰግዱና ሴቶችም ሒጃብና ኒቃብ እንዳይለብሱ ከከለከለ ብሁዋላ መሆኑ ቷውቋል፣
አንዳንዳን ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሆኖው ትምህርታቸውን በማቋረጥ ተቃውማቸውን በመግለጽ ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ጋር ተገናኝተው ለመነጋገር ያደረጉት ሙከራ ከበላይ አካል የመጣ ትእዛዝ ነው ምንም ማድረግ አይቻልም በሚል እንዳልተሳካላቸው ጠቅሰው በአሁኑ ግዜ ግቢውን ጥለን ከመውጣት ውጭ ሌላ አማራጭ የለንም ሲሉ ተደምጠዋል፣
በዩኒቨርሲቲው ግቢ እንዳንሰግድ መከልከሉ ስርዓቱ የተማሪው ፤ የሞስሊሙ ማህበረሰብና በአጠቃላይ በሃገሪቱ እየታየ ባለው ተቃውሞ ውጥረት ውስጥ ስለገባ ነው ሲሉ አንዳንድ የግቢው ተማሪዎች አክለው ገልጸዋል፣