Wednesday, February 19, 2014

የህወሃትና ኢህአዴግ ካድሬዎች በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞንና ምእራባዊ ዞን ውስጥ ለሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች በሽሬ ከተማ ውስጥ ሰብስበው ፀረ ሙስና የሚል አርእስት በማንሳት ትምህርት እየሰጥዋቸው መሆኑን ለማወቅ ተችለዋል።



በትግራይ ክልል ምእራባዊና ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ውስጥ ለሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች የስርአቱ ካድሬዎች በሽሬ ከተማ ሰብስበው ፀረ ሙስና የሚል አርእስት በማንሳት እያስተማርዋቸው እንደሆኑ የገለፀው መረጃው እድሜያቸው የደረሱ ወጣቶች ግን በስብሰባው እንዳልተካፈሉ ተገልፀዋል።
መረጃው በማስከተል እድሜያቸው ለደረሱ ወጣቶች በስብሰባው ላይ እንዳይሳተፉ የተደረገው ዋነኛው ምክንያት። በአገራችን ውስጥ በኢህአዴግ  ባለስልጣናት እየተፈፀመ ያለውን የሃብት ማጠፋፋት ተግባር ስለሚያውቁትና ይህንን አስመልክተው ጥያቄዎችን በማንሳት እንዳያጋልጡዋቸው በማሰብ እንደሆነና ምንም ዓይነት እውቅት ለሌላቸው ታዳጊ ወጣቶች አስተማርናቸዋል በማለት በሰበቡ የቀን ውሎ ኣበል ለማግኘት ያካሄዱት ስብሰባ እንደሆነ መረጃው አስታውቀዋል።
ይህንን ዓይነት ተንኮል የተሞላበት የስርዓቱ አስነዋሪ ተግባር ለአቅመ ኣዳም ላልደረሱ ወጣቶች በማደናገር የስርዓቱን እድሜ ለማራዘም ታስቦ የተፈፀመ እንደሆነ የሽሬ ከተማና የአካባቢው ህዝብ እየገለፀ መሆኑን ከዞኑ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድተዋል።