የግምገማው አጀንዳ ሰራዊቱ ለምን ይከዳል? የሚል ሆኖ የእዙ ከፍተኛ አመራሮች ቀደም ብለው በጉዳዩ ከተወያዩበት
ብሁዋላ በየደረጃው ወደ ሰራዊቱ እንዲወርድ የተደረገ ነው፣ የበታች አመራሮችን ጨምሮ ተራ ወታደሩ ለቀረበው ግምገማ ትኩረት እንዳልሰጡት
ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በማእከላዊ እዝ የ 33ኛ ክ/ጦር አባላት የሆኑ ወ/ር መሓመድ ዓሊና ወ/ር ነጊሶን
ስርዓቱ ያስታጠቃቸውን ብረት በመሸጥ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲሄዱ በሽራሮ ከተማ ተይዘው በእስር ላይ ይገኛሉ፣ ወታደሮቹን ለክዳት የገፋፋቸው
ዋና ምክንያት በመከላከያ የሰራዊት መተዳደሪያ ደምብ መሰረት አገልግሎታቸውን ከፈጸሙ ብሁዋላ ከሰራዊቱ የመሰናባት መብታቸው ባለመከበሩና
በተደጋጋሚ የስንብት ጥያቄ አቅርበውም ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ተገቢውን መልስ ማግኘት ባለምቻላቸው መሆኑ ከቦታው የደረሰን ዘገባ
ቸምሮ ያስረዳል፣