በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ፤ በታሕታይ አድያቦ ወረዳ፤ ዓዲ-ኮኾብ በተባለ አከባቢ የሚገኙ የማእከላዊ እዝ
አባላት የሆኑ ወታደሮች በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ብልሹ አሰራር የፈጠረው ልዩነትና አድልዎ መቋቋም ስላልቻሉ ከሰራዊቱ ለመክዳት እየተገደዱ
መሆኑ የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።
በደረሰን ዘገባ መሰረት በመላ አገሪቱ በተለይ በትግራይና በአፋር ክልል የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት
የአምባገነኑ ስርዓት አገልጋይ ሆኖው የመቀጠል ፍላጎት ስለሌላቸው ሰራዊቱን በመክዳት ወደ መረጡት ቦታ በመሄድ ላይ ይገኛሉ። ሁኔታው
የኢህአደግን ስርዓት ውድቀት ያመለክታል ሲሉ የሰራዊቱ አባላት ይደመጣሉ።
ቀደም ሲል ባቀረብነው የዜና ዘገባ በማእከላዊ እዝ ብቻ ሰራዊቱን ሲከዱ ተገኝተዋል በሚል በሽረ-እንዳስላሰ
ከ 2000 በላይ ወታደሮች በእስር ላይ እንደሚገኙ መዘገባችን የሚታወስ ነው።