Tuesday, January 29, 2013

የማእከላዊ እዝ የተዋጊ አውሮፕላኖችን ፤ የከባድ መሳሪያዎችንና የእግረኛ ሰራዊትን ያካተተ የተቀናጀ ወታደራዊ ልምምድ 26 ጥር 2005 ዓ/ም ለማድረግ እንደተዘጋጀ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በመከላከያ ሰራዊት ባጠቃላይ በተለይም ከማእከላዊ እዝ የኢህአደግ ስርዓትን በመቃወም የሚከዱ ወታደሮች ቁጥር ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ በመጣበት በአሁኑ ወቅት እንዲህ አይነቱ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ የተፈለገው የሰራዊቱን አባላትንና የአከባቢውን ህዝብ ቀልብ ለመጠምዘዝና አለሁ ለማለት ነው ሲሉ የእዙ የሰራዊት አባላት ይናገራሉ፣
በደረሰን ዘገባ መሰረት በልምምዱ ወቅት ጄነራል ሳሞራ ዮኑስ የሚገኝ ሲሆን 27 ጥር 2005 ዓ/ም የልምምዱን መጠናቀቅ ተከትሎ ዓዲ-ቦኽራይ በተባለ ልዩ ቦታ ደማቅ ድግስ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችለዋል፣