Tuesday, January 29, 2013

በአማራ ክልል ፤ በአዊ ዞን ፤ በጓጉሳ ወረዳ ፤ የቅዳመሓጃ ቀበሌ ኗሪ ህዝብ ካለፍላጎት በማስገደድ የሚሰራ የውሃና አፈር ጥበቃ ስራን ተቃወመ፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት ከጥር 12-18,2005 ዓ/ም ብርሃኑ በተባለ የጓጉሳ ወረዳ የግብርና ቢሮ ሃላፊ የቀረበ ህዝብን አስገድዶ በውሃና አፈር ጥበቃ ስራ የማሰማራት ሙከራ በአከባቢው ህዝብ ተቀባይነት አለማግኘቱንና ህዝባዊ ተቃውሞም መቀስቀሱን ቷውቋል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በአንከሻ ወረዳ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና በውሃና አፈር ጥበቃ ከ ጥር 10 ጀምሮ ለሦስት ቀናት ሊካሄድ የታሰበ ስብሰባ ያለውጤት ተበትናል፣
ስብሰባው በወረዳዋ የተፈጥሮ ሃብት ሃላፊ አቶ ጌትየ ሁነኝ የተመራ ሲሆን በስብሰባው ህዝቡ የውሃና አፈር ጥበቃና ስራ እንዲሰራና የምርጫ ካርድም የግድ እንዲወስድ ማድረግ የሚል አጀንዳ ከቀረበ ብሁዋላ ህዝቡ በመቃወሙና ስብሰባውንም ረግጦ ስለወጣ በሦስት ቀናት እንዲጠቃለል እቅድ ተይዞለት የነበረ ስብሰባ ከግማሽ ቀን ብሁዋላ መበተኑን ዘገባው ጨምሮ ያስረዳል፣