Thursday, January 31, 2013

በትግራይ ክልል በነባርና አዲስ የፖሊስ አባላት መካከል ቅራኔ መፈጠሩ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት በሁለቱም የፖሊስ አባላት መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት ነባር የፖሊስ አባላት በትምህርት ደረጃ ዝቅ ያሉና በእድሜም ገፋ ያሉ የህወሓት ታጋዮች የነበሩ ሲሆኑ አዳዳስ የፖሊስ አባላት ደግሞ ባላቸው የትምህርት ደረጃ ምክንያት የተሻለ ቦታ ስለሚሰጣቸው ነባረቹ በአዲሶች ተውጠናል የሚል ስሜት የፈጠረው መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል፣
ለአዲስ የፖሊስ አባላት የተለያዩ የሞያ ስልጠናንና ሃላፊነት ሲሰጣቸው ነባር የፖሊስ አባላት ደግሞ ከስራ ሲሰናበቱና በተራ ስራ ተመድበው እንዲሰሩ ስለሚደረግ በመካከላቸው የተፈጠረ የጥቅም ቅራኔ ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ በመሄድ ላይ መሆኑን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣