Monday, January 21, 2013

በማእከላዊ እዝ ፤ በ 31ኛ ክ/ጦር ፤ የ2ኛ ሬጅመንት አባል የነበረ አንድ ወታደር አንድ መ/አ ገድሎ እራሱን አጠፋ።



ወታደሩ ወደ ውትድርና ሞያ ሲገባ በኮምዩተር ሞያ ስልጥኖ በሰለጠነበት ሞያ ተመድቦ እንደሚሰራ ተነግሮት የገባ ሲሆን ነገር ግን በቃል የተነገረውንና በተግባር የጠበቀው ስራ ለየ ቅል ሆኖበት ቅር ቢሰኝም ውልን እስኪጨርስ ድረስ በተመደበበት ቦታ ሲያገለግል ቆይቷል። በውሉ መሰረት 7 ዓመት በጦሩ ካገለገለ ብሁዋላ በህጉ መሰረት የስንብት ጥያቄ አቅርቦ በመከልከሉ ምክንያት ታህሳስ 29,2005 ዓ/ም ለሊት ባድመ በሚገኘው ጦሩ የመሸገበት አንድ ተራራ ላይ አንድ የመ/አ ገድል እራሱን ማጥፋቱን ከሬጅመንታ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
እንዲህ ዓይነቱ ፍጻሜ በሁሉም የመከላከያ ክፍሎች እየታየ በመምጣቱ በከፍተኛ የሰራዊቱ አዛዦች ላይ ከፍተኛ ጭንቀት መፈጠሩ ለማወቅ ተችለዋል።
ቀደም ሲል እራሳቸውን ለመግደል ባደረጉት ሙከራ ቆስለው የተረፉ በርካታ ወታደሮች በዓዲ-ኮኾብ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙ መሰገባችን የሚታወስ ነው።