Tuesday, January 29, 2013

በሸራሮ ከተማ የማጽዳት ግምገማ በሚል በከተማዋ ኗሪ ህዝብ ላይ እየተካሄደ ያለ በህወሓት ካድሬዎች የተመራ ግምገማ በነባር ታጋዮች ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ቷውቋል፣



በከተማዋ የተካሄደው የዩስሙላ ግምገማ ለስርዓቱ ከፍተኛ ካድሬዎችንና በየደረጃው ላሉት ባለስልጣናትን የማይመለከት ሆኖ በግል ስራ ተሰማርተው ህይወታቸውን በመምራት ላይ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ የሚያነጣጥር ነው፣
በተለይም ከህወሓት ተሰናብተው በአሁኑ ግዜ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው የግል ኑራቸውን በመምራት ላይ የሚገኙ ነባር የህወሓት አባላትን ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ግንኝነት አላችሁ በሚል ሰበብ ቀደም ሲል እራሳችውን እንዲከላከሉበት በድርጅቱ የተሰጣቸውን ሽጉጥ እንዲያስረክቡ እየተደረገ መሆኑ ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
በደረሰን ዘገባ መሰረት በረከት የተባለና ሌላ ለግዜው ስሙ ያልተገለጸ ነባር የህወሓት ታጋይ ከተቀዋሚ ድርጅቶች ጋር ግንኝነት አላችሁ ፤ ህወሓትንና መንግስትን በመጻረር ትንቀሳቀሳላችሁ በሚል ለብዙ ዓመታት ይዘውት የነበረውን ሽጉጥ ተነጥቀዋል ፣ ሁኔታው ህወሓት ምን ያህል ከህዝብ እንደተነጠለ የሚያሳይ ሆኖ የከተማዋ ኗሪዎችንም በሰፊው እያነጋገረ ያለ ጉዳይ መሆኑን ለማወቅ ተችለዋል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በሸራሮ ከተማ አስተዳደር አቶ ጥላሁን በርሀ በወረደ ቀጥተኛ መመሪያ መሰረት ማንኛውም የምርጫ ካርድ ያልወሰደ የከተማዋ ኗሪ የህክምና አገልግሎትን ጨምሮ መንግስት ገበያን ለማረጋጋት በሚል የሚያቀርበውን እንደ ዘይት ፤ ስኳር የመሳሰሉ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን እንዳይገዛ መከልከሉን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል ፣