Tuesday, January 29, 2013

በትግራይ ክልል የምርጫ ካርድ የወሰደው ህዝብ ቁጥር ከተጠበቀው በታች መሆን የህወሓትን አመራሮች አሳስቧል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት በአክሱም ከተማና አከባቢዋ በሚገኙ መንደሮች ካሉ ኗሪዎች መካከል 5000 ህዝብ ብቻ የምርጫ ካርድ ወስዷል፣ ሁኔታው የህወሓት የስልጣን ቆይታ አደጋ ላይ መሆኑን የሚያመላክት ነው ሲሉ የአከባቢው ኗሪዎች ይናገራሉ፣
በአክሱም ከተማና አከባቢዋ የምርጫ ካርድ ለመውሰድ የተመዘገበው የህዝብ ቁጥር ዝቅተኛ መሆን የህወሓት ቀጣይነት አደጋ ላይ የሚጥልና የስርዓቱንም ውድቀት የሚያፋጥን በመሆኑ ጉዳዩ የክልሉን መስተዳድር ሳያሳስብ አልቀርም፣ በዚህም የክልሉ መስተዳድር ከክልሉ የተወከሉ ባለስልጣናት ወደ አክሱም ከተማ በመላክ ህዝቡን ለመቀስቀስ ያደረገው ሙከራ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ባለማግኘቱ የተነሳ እንዳልተሳካ ለማወቅ ተችለዋል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በትግራይ ማእከላዊ ዞን የተምቤን ከተማ ኗሪ ህዝብ የምርጫ ካርድ ባለመውሰዱ ምክንያት በአምባገነኑ ስርዓት የሚደርስበትን ጫና በመቃወም የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ መሆኑ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
በተመሳሳይ በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ የምርጫ ካርድን ያልወሰዱ ተማሪዎች ከፈተና መታገድን ጨምሮ የሚያነሳቸው ሌሎች ጥያቄዎችንም ምላሽ እንደማያገኙ የተነገራቸው ሲሆን በከተማዋ የሚገኙ የፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላትም የሲቪል ልብስ ለብሰው የምርጫ ካርድ እዲወስዱ እየተደረገ መሆኑ ቷውቋል፣