Tuesday, January 29, 2013

በትግራይ ማእከላዊ ዞን ፤ በታሕታይ ማይጨው ወረዳ ፤ በውቕሮ ማራይ ከተማ በሙስና የተጨማለቁ የከተማዋ የመስተዳድር አካላት ከህዝብ እየተሰወሩ መሆኑ ቷውቋል፣



ለህዝብ ተብሎ የተላከ 100 ኩንታል የፈርኖ ዱቄትና 60 ኩንታል ማዳበርያ ሸጦ ለግል ጥቅሙ ያዋለው ቄስ ሓድሽ ገ/መድህን የተባለ የከተማዋ የመስተዳድር አካል ፤ የአከባቢው ህዝብ ሁኔታውን እንደደረሰበትና እየተከታተለው መሆኑን ስላወቀ ከአከባቢው መሰወሩን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣
በተመሳሳይ በሸራሮ ከተማ የግብርና ቢሮ ሰራተኛ ሚኪኤለ ተስፋሁነይ የተባለ ግለሰብ ከታሕታይ አድያቦ ወረዳ የመስተዳድር አካላት ጋር በመመሳጠር ለህዝብ ተብሎ የመጣ 300 ኩንታል ስንዴ ወደ ዓዲ-ሃገራይ ወስዶ በሸጥ ለግል ጥቅሙ እንደአዋለው ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል ፣
ግለሰቡ ከአከባቢው ጸረ-ህዝብ የመስተዳድር አካላት ጋር በመመሳጠር ወንጀሉን ሲፈጽም በህዝቡ እጅ ከፈንጅ ተይዞ ወደ ህግ ቢቀርብም ጉዳዩ በሙስና ከተጨማለቁት የከተማዋ የመስተዳድር አካላት ጋር የተያያዘ በመሆኑ ከሦስት ቀናት እስራት ብሁዋላ ወንጀለኛው ነጻ ተለቋል፣
ድርጊቱ በከተማዋ የህዝብ ቁጣን መቀስቀሱን ለማወቅ ተችለዋል፣