ግጭቱ የተቀሰቀሰው የግድቡ የግምባታ ስራ በሚካሄድበት አከባቢ በጥበቃ ስራ የተሰማሩ የፈዴራል ፖሊስ አባላት
ወደ ግድብ ለመግባት ከመጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር እንገባለን አትገቡም የሚል ንትርክ በመነሳቱ ምክንያት በመሃከላቸው ጠብ
ተፈጥሮ በብረትና በድንጋይ መደባደባቸውን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣
በደረሰን ዘገባ መሰረት በግጭቱ ምክንያት ከፌደራል ፖሊስ 3 አባልት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶ በአስጊ ሁኔታ
ላይ የሚገኙ ሲሆን በሌሎች 3 ላይ ቀላል ጉዳት ደርሳል፣ በተመሳሳይ በመከላከያ ሰራዊት 2 አባላት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶ በአስጊ
ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሲሆን በሌሎች 4 አባላት ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችለዋል፣