በደረሰን ዘገባ መሰረት በሑመራ ከተማ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ከተለያዩ የሃገሪቱ አከባቢ ስራ ፍለጋ የመጡ
የቀን ሰራተኞች የሚገኙ ሲሆን የከተማዋ የመስተዳድር አካላትና የስርዓቱ ካድሬዎች የቀን ስራተኞቹ ወደ አከባቢያቸው ተመልሰው በመሄድ
በሚያዝያ ወር 2005 ዓ/ም በሚደረገው የአከባቢና የሟሟያ ምርጫ የግድ እንዲሳተፉ ለማድረግ እስራትን ጨምሮ በሰራተኞቹ ላይ የተለያዩ
ጫናዎች እያደረጉ መሆኑ ቷውቋል፣
ወደ አከባቢያቸው ተመልሰው በምርጫው ለመሳተፍ ፈቃደኛ አይደሉም በሚል አብዛኛዎቹ ሰራተኞች የታሰሩ ሲሆን
ከነዚሁ በምርጫ ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑትን ግን በዋስ ተለቀው ወደ አከባቢያቸው እንዲሄዱ እየተደረገ ነው፣
የሰራተኞቹን መታሰር ተከትሎ በከተማዋ ተቃውሞ ይቀሰቀሳል የሚል ስጋት እየተጠናከረ መምጣቱ ከቦታው የደረሰን
ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣