Sunday, February 17, 2013

በትግራይ ክልል አዲስ የፖሊስ አባላትን ለመመልመል የተደረገው ሙከራ የክልሉ ተማሪዎችና ወጣቶች እንዳልተቀበሉት ቷውቋል ፣



የክልሉ የፖሊስ ጽ/ቤት አዲስ የፖሊስ አባላትን ለመመልመል ማስታወቅያ ቢያወጣም የክልሉ ወጣቶች የፖሊስ አባላት የባለስልጣናት የግል ንብረት ሲጠብቁና ህዝብን ሲጨፈጭፉ እንጂ ህግና ስርዓትን ሲያስከብሩና ህዝብን ሲያገለግሉ አላየንም በማለት ምልመላውን መቃወማቸውን ከተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
ይህ በእንዲህ እያለ አዲስ የፖሊስ አባላትን ለመመልመል ወደ ተለያዩ የክልሉ አከባቢዎች የተላኩ የክልሉ የፖሊስ ጽ/ቤት ባልደረቦች ተልእኳቸውን ሳይፈጽሙ መመለሳቸውን ተከትሎ ወጣቱ ለምን ምልመላውን ተቃወመው የሚሉ ጥያቄዎች በፖሊስ አባት በየደረጃው ላሉ አመራሮች መቅረብ መጀመሩን ለማወቅ ተችለዋል ፣
አምባገነኑ የኢህአደግ መንግስት የሚያስተዳድረው የፖሊስ ሃይል ህዝባዊነትን ያልተላበሰ ህገመንግስቱ ከሚፈቅደው ውጭ ለኢህአደግ ህልውና የቆመና በህዝብ ላይ በደል የሚፈጽም በመሆኑ ወጣቶቹ በክልሉ መንግስት የወጣውን አዲስ የፖሊስ አባላትን መመልመል የተመለከተ ማስታወቅያ በመቃወም የወሰዱት እርምጃ የሚደገፍ ነው ሲሉ አንዳንድ ወገኖች ይገልጻሉ፣