Friday, February 1, 2013

በዳውሮ ዞን ተቃውሞ ቀስቅሰዋል የተባሉ ግለሰቦች መታሰራቸውን ለማውቅ ተችለዋል፣



በዳውሮ ዞን ፤ በማረቃ ወረዳ ፤ በወረዳዋና በክልል ከማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ ለተፈጠረው ግጭት መርተዋል በሚል አቶ ዱባለ ገበየሁ ፤ አቶ ጎሳሁን ዶሳ ዶሻንና አቶ ግዛቸው ታደሰ ከበደ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቷውቋል፣
አቶ ዱባለ ገበየሁ ቀደም ሲል የደኢህደግ አባል የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ግዜ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች አባልና የድርጅቱ የደቡብ ክልል ተወካይ ናቸው፣
አቶ ዱባለ የደኢህደግ አባል በነበሩበት ግዜ በወቅቱ የክልሉ ምክትል ፕረዚዳንትና የደኢህደግ የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ የነበሩ አቶ አለማዮሁ አሰፋን የመንግስትን ስልጣን ተግን በማድረግ ዘመዶቻቸውን እየሾሙ ነው በሚል ገምግመዋቸው እንደነበረ አስታውሰው አሁን በላያቸው ላይ እየተፈጸመ ያለው በደልም መነሻው ከዚሁ ጋር ተያይዞ የመጣ ቂም በቀል መሆኑን አስረድተዋል፣ በአሁኑ ግዜ የማረቃ ወረዳ ዓቃቢ ህግ ከእርሳቸው ጋር በእስር ቤት እንደሚገኙ አቶ ዱባለ ጨምረው ገልጸዋል፣
በማረቃ ወረዳ ማሪ በተባለ አከባቢ ባለፈው ሳምንት በተቀሰቀሰው የህዝብ አመጽ ሻለቃ በዛብህ ገዝሙ የተባለ የዞኑ ፖሊስ የበላይ አመራርና አንድ ወታደር በድንጋይ ሲቀጠቀጡ አንድ የመንግስት ተሽከርካሪ ተሰባብሮ ከጥቅም ውጭ መደረጉንና የመኪናን መንገድ በመዝጋትም የትራንስፖርት አገልግሎት ለግዜው እንዲሰናከል መድረጉን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣
የማሪናንና የዋካን ህዝብ እንዲጋጭ እያደረገ ያለው መንግስት ነው ሲሉ የስርዓቱ ካድሬዎች ይናገራሉ፣ ካለፉት ቀናት ጀምሮ አከባቢው በየፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ታውቋል ፣