Friday, February 1, 2013

የኢህአድግ ስርዓት በስመ ኢንቨስትመንት የድሃውን ገበሬ መሬት እየቀማ ለባለሃብቶች መስጠት መቀጠሉ ከአዊ ዞን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት ‘አየሁ የእርሻ ልማት’ ለተባለ የሸክ አላሙዲ ካምፓኒ የተመረጠ የእርሻ መሬት ለመስጠት በአከባቢው ላለፉት 60 ዓመታት በእርሻ ሲተዳደሩ የነበሩ ገበሬዎች ከቀያቸው እንዲፈናቀሉና ቤታቸውንም እንዲፈርስ እየተደረገ መሆኑ ቷውቋል፣
ተበዳዮቹ መፍትሄ ፍለጋ ወደ ዞን መስተዳድር በመሄድ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዘዘውን ቢያነጋግሩም የታዘዛችሁትን ፈጽሙ የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፣ በዞኑ መስተዳድር ምላሽ ያልተደሰቱት የአከባቢው ኗሪዎች ከመካከላቸው ሰዎችን በመወከል እስከ ፌደራል መንግስት ድረስ በመሄድ ቅሬታቸውን ቢያቀርቡም የተለይ ምላሽ ባለማግኘታቸው ተስፋ ቆርጠው ወደ አከባቢያቸው መመለሳቸውን ለማወቅ ተችለዋል ፣
በስመ ኢንቨስትመንት ገበሬውን ከቀየው እያፈናቀሉ የተረጋጋ ህይወት እንዳይኖረው በማድረግ ለድህነት ፤ ለበሽታና ሞት መዳረግ በኢህአደግ ዘመን የተለመደ ተግባር መሆኑ የሚታወቅ ነው፣