Sunday, February 17, 2013

የብአዴን-ኢህአደግ ስርዓት በምዕራብ ጎጃም ዞን ወምበርማ ወረዳ የሚኖሩ ገበሬዎችን ካለፍላጎታቸው የገዥው ፓርቲ ልሳን የሆነው “አዲስ ራኢ” እንዲገዙ እያስገደዳቸው መሆኑንን ቷውቋል፣




የአማራ ክልል መስተዳድር እስከ ታች ድረስ ባወረደው መመሪያ መሰረት የክልሉን ገበሬዎች በልማት ቡዱን ስም በማደራጀት የኢህአደግን የፖለቲካ አስተሳሰብ ለማስፋፋት ይጠቀሙበታል፣ የወንበርማ አስተዳዳሪ አቶ ጌትነት አደረጃጀቱን በመጠቀም የወረዳዋን ገበሬዎች የኢህአደግ ልሳን የሆነውን “አዲስ ራኢ” ካለፍላጎታቸው ተገደው እንዲገዙ እያደረገ መሆኑ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በወረዳዋ የሚገኙ የባልነት መዋጮ መክፈልን የተቃወሙ የብአዴን-ኢህአዴግ አባላት በድሪጅቱ አመራሮች ጫና እየተደረገባቸው መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል፣
አባላቱ መዋጨውን መክፈል ካልቻሉ በውንበርማ ወረዳ ለሚገኙ ቀበሌዎች የተመደበው የመንግስት በጀት ተቆርጦ ለብአዴን ገቢ እንዲደረግ በመወሰኑ ምክንያት የአከባቢው ኗሪ ህዝብ ተቃውመውን በመግለጽ ላይ ሲሆን ለጤና አገልግሎት ተብሎ ከበጎ አድራጎት የተገኘ ገንዘብም ለወረዳዋ የካብኔ አባላት አበል ወጪ እንዲሆን በማድረግ በወረዳው ህዝብ ስም በርዳታ የተገኘውን ገንዘብ አለአግባብ እያባከኑት መሆኑን የደረሰ ዘገባ ያስረዳል ፣