Saturday, May 25, 2013

ባለፈው ሳምንት ከታሰሩት 20 የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል ዘጠኙ ሲፈቱ ቀሪዎቹ አሁንም እስር ላይ መሆናቸውን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣፣



ባለፈው ሳምንት የተለያዩ ጥያቄዎችን በመያዝ ትምህርት በማቋረጥ በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የተደረገው አድማ ተከትሎ ከታሰሩት 20 ተማሪዎች መካከል ዘጠኙ የተፈቱ ሲሆን ቀሪዎቹ ገና እስር ላይ መሆናቸውን የተገነዘቡ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ገና በእስር ላይ የሚገኙትን ተማሪዎች መፈታትን ጨምሮ ለጥያቄዎቻቸው መልስ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ባሉበት ሰዓት የፌደራል ፖሊስ ወደ ዩኒቨርሲቲው ግቢ ጥሶ በመግባት ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን የግድ እንዲቀጥሉ በየመኝታ ክፍላቸው ሳይቀር እየገቡ ድብደባ በመፈጸም በተማሪዎቹ ላይ ጫና በማድረግ ላይ ናቸው፣፣
በያዝነው ሳምንት በአርባምንጭ አከባቢ በሚገኙ የጨገግ ፤ ሳውላና ቁጮ ወረዳዎች የተቃዋሚዎች በራሪ ጽሁፍ ተበትኖ ተገኝታል፣፣ በሁኔታው ቅር የተሰኙ የአከባቢው የኢህአዴግ ባለስልጣናት ጽሁፉን የጻፈው ማነው ? ፤ ጽሁፍን የበተነ ሰው በውስጣችሁ ደብቃችኃል ፤ አጋልጡት ፤ አስወጡት ውደ ህገ እንድታቀርቡት የናንተን እርዳታ እንጠብቃለን በማለት በኗሪው ህዝብ ላይ ጫና በማድረግ ኗሪውን በስብሰባ ጠምደውት ይገኛሉ፣፣
በተበተኑት በራሪ ወረቀቶች ምክንያት ሊረጋጉ ያልቻሉ የአከባቢው የመስተዳድርና የጸጥታ አካላት በከተማው ህዝብ ላይ እያደረጉት ካለው ጫና በተጨማሪ ወደ ወረዳዎቹ የሚገቡና የሚወጡ ተሽከርካሪዎችን በጥብቅ እየተፈተሹ እንዲያልፉ እየተደረገ መሆኑ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣
በሌላ በኩል ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል በማድረግ ላይ የሚገኝው ሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን ጉንበት 15/2005 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ጀምራል፣ ጉባኤውን የመሩት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ሲሆኑ በጉባኤው በእስር ላይ ሰለሚገኙት ጋዜጤኞችና የተቃዋሚ ድርጅት አባላት ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ፤ ከቤንሻንጉል ክልል ተፈናቅለው የነበሩና ዳግም ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የተደረጉት የብሄር አማራ ተወላጆች ጉዳይ ፤ በየዩኒቨርሲቲ በተደጋጋሚ የሚቀስቀሱ ግጭቶች ለምን መፍትሄ አይደረግላቸውም ? የሚሉና ሌሎች ጉዳዮች በስብሰባው ቱክረት ከሚደረግባቸው ዋና ዋና ነጥቦች መሆናቸውን ከድርጅቱ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፣፣