Saturday, May 25, 2013

በያዝነው ዓመት የተመረቁ አዲስ የፌደራል ፖሊስ ምልምሎች ከተመደቡበት ክፍል ለጠፉና ለከዱ ነባር የፌደራል ፖሊስ አባላትን ለመተካት የህዳሴው ዲቪዥን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የሃገሪቱ አከባቢዎች እየተመደቡ ነው፣፣



በ 2005 ዓ/ም አዲስ ተመርቀው ከወጡት የፌደራል ፖሊስ ምልምሎች እስከ ሻለቃ የሚገኙባቸው 85 አዲስ ሰልጥነው የወጡ ምልምሎች በመገንባት ላይ ላለው የህዳሴ ግድብ እንዲጠብቅ በአከባቢው ከተሰማራው የህዳሴ ዲቪዥን በክህደት የጠፉትን ነባር የፌደራል ፖሊስ አባላትን ለመተካት ወደ አሃዱው መመደባቸውንና በአንድ ሃይል እስከ 35 የሚደርስ የሰው ሃይል መመደቡን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣፣
በደረሰን ዘገባ መሰረት አዲስ የተመረቁት የፌደራል ፖሊስ አባላት በቦታው ሲደርሱ በህዳሴው ዲቪዥን አዛዥ ኮማንደር ኪሮስ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ኮማንደሩ በንግግራቸው በባህር ዳር ከተማ በአንድ የፌደራል ፖሊስ ባልደረባ በከተማዋ ኗሪዎች ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ መደገም የለበትም ሲሉ አሳስበዋል፣፣
በህዳሴው ግድብ በጥበቃ ስራ ላይ የነበረች አንዲት ጋንታ(ጋንታ-4) ወደ አዲስ አበባ በዝውውር መሄዳንም የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣፣