በደረሰን ዘገባ መሰረት ኢህአዴግ እየተከተለው ባለ ሃላፊነት የጎደለው አሰራር በዚች ታሪካዊትና ጥንታዊት
የጎንደር ከተማ ህግና ስርዓት ጠፍቶ ኗሪዎቻ በመኖሪያ አከባቢ ይሁን ከቦታ ቦታ በስጋት ይንቀሳቀሳሉ፣፣ በከተማዋ የፖሊስ አባላት
የሚገኙበት የተደራጁ ዘራፊዎች ጉንበት 9,2005 ዓ/ም የአቶ አንዳርጌ የተባሉ የከተማዋ ኗሪ ግለሰብ ሱቅን ሰብረው በመግባት ከ
20 ሽህ በላይ የሚገመት ንብረትና ጥሬ ገንዘብ መዝረፋቸውን ቷውቋል፣፣
ይህ በእንዲህ እያለ የመተማ ከተማ የጉምሩክ ሰራተኞች ጉንበት 10,2005 ዓ/ም አቶ ታፈሰ አለባቸው የተባለ
ኗሪነቱ በአከባቢው የሆነ ግለሰብ የእርሻ መሳሪያውን ጭኖ ወደ እርሻው በመሄድ ላይ በነበረበት ግዜ መኪናውን በማቆም ንብረቱን እንደዘረፉት
ለማወቅ ተችሏል፣፣
አቶ አለባቸው የተዘረፈውን ንብረት ለማስመለስ በጎንደር ከተማ ወደ ሚገኘው የጉምሩክ ጽ/ቤት በመሄድ ቢያመለክትም
በስሙ የተመዘገበ የተወረሰ ንበረት እንደማያውቁና ከጽ/ቤቱ ለግለሰቡ የሚመለስ ንብረት የለም በማለት እንዳሰናበቱት የደረሰን ዘገባ
ጨምሮ ያስረዳል፣፣