እነዚህ በቋራ ወረዳ በማህበር ተደራጅተው በእጣን ለቀማ ስራ እንዲሰማሩና ያመረቱትን እጣን መንግስት እንዲገዛቸው
ተነጋግረው ወደ ስራ የገቡ ወጣቶች ጉልበታቸውንና ገንዘባችውን በማፍሰስ ያጠራቀሙትን የእጣን ምርት መንግስት በገባላቸው ውል መሰረት
ሊረከባቸው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለኪሳራ መዳረጋቸውን ቷውቋል።
ወጣቶቹ
ብርድና ጸሃይ እየተፈራረቁባቸው በከፍተኛ ድካምና ልፋት ያመረቱትን እጣን በገቡት ውል መስረት መንግስት እንዲረከባቸውና ከኪሳራ
እንዲወጡ በሰላማዊ ሰልፍ ቢጠይቁም እስካሁን ድረስ በመንግስት የተሰጣቸው ምንም ዓይነት ምላሽ እንደሌለ ሰላማዊ ሰልፉን ያስተባበሩትና
የማህበሩ ሃላፊ የሆኑ አቶ ንጉሰ አበጋዝ ገልጸዋል።