በደረሰን ዘገባ መሰረት በወልቃይት ወረዳ እየተገነባ ላለው የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት ተብሎ በሁለት መኪናዎች
ተጭኖ የተላከ ተንዲኖ ፤ ስሚንቶና ጣውላ በባህርዳር ከተማ ከደረሰ ብሁዋላ ኗሪነታቸው በከተማዋ ለሆኑ አቶ መንግስቱ ለተባሉ ነጋዴ ተሽጦ በመራገፍ ላይ እያለ ሃምሌ
1,2005 ዓ/ም እጅ ከፈንጅ መያዙን ቷውቋል።
የተሸጠውን ንብረቱን በአቶ መንግስቱ መጋዝን ሲያራግፉ የነበሩ ተሽከርካሪዎች የሰሌዳ ቁጥር 30816 እና
11019 ሲሆን በህዝብ ትብብር ተይዘው ወዲያውኑ ፖሊስ እንዲረከባቸው ቢደረግም ፥ተጠርጣሪዎቹ ሆነ ተሽከርካሪዎቹ ያለምንም ማጣራት
ተለቀዋል።
ይህ በእንዲህ
እያለ በአማራ ክልል በወረኢሉ ወረዳ ለአከባቢው ህብረተሰቡ እርዳታ ተብሎ የተላከ ከ 7000 ኩንታል በላይ እህል የወረዳዋ አስተዳደር
አቶ አበበ አዲሱ ከሌሎች ግበረአበሩ ጋር ሆኖ በመዝረፍ ለግሉ ጥቅሙ አውሎት ሲያበቃ ከሦስት ቀናት ብሁዋላ ተመልሶ መጋዝኑ ተዘረፈ
በማለት ለሚመለከተው የመንግስት አካል ሪፖርት አድርጓል ። የአከባቢው ኗሪ ህዝብ ግን መጋዝኑን የዘረፈው እራሱ አሰዳደሩ ነው በማለት
አስተዳደር ተብየው ወደ ፍትህ እንዲቀርብ በመጠየቅ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።