በምእራባዊ ትግራይ ዞን
በሁመራ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ህጋዊ መንገድ ተጠቅመው ቁርስና ሻሂ ቤቶች በመክፈት ኑሮኣቸው እየመሩ የቆዩ በርከት ያሉ ወገኖች።
በአሁኑ ግዜ በገበያ ውስጥ የስኳር እጥረት በመከሰቱ ምክንያት የንግድ ድርጅቶቻቸውን የዘጉ ወገኖች። ኑሮኣቸው በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ
እንዳለ። ከከተማዋ የደረሰን መረጃ አስታወቀ፣
እነዚህ ካላቸው ገቢ ከተገቢው በላይ ለመንግስት ግብር በመክፈል በንግድ
ሥራ ላይ ተሰማርተው የቆዩና። በስኳር እጥረት ምክንያት ድርጅታቸውን
የዘጉ አብዛኛዎቹ ሴቶች መሆናቸውንና። ሲሰሩበት ከነበረ ሻይ ቤትና ቅርስ ቤት ሌላ አማራጭ ሥር ባለመኖሩ። አጋጥሞ ባለው የስኳር
እጦት ምክንያት ጠቅልለው ከሥራ ውጭ ሆነው እንዳሉና። እለታዊ ኑሮኣቸው መምራት እንደተሳናቸው የደረሰን መረጃ ገለፀ፣
ስልጣን ላይ ያለው ህዝባዊ ወገንተኝነት የሌለው የህወሓት ኢህአዴግ ስርአት።
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የስኳር አቅርቦት አገር ውስጥ ባሉ ፋብሪካዎች ሊማሉ ይችላሉ በማለት ከውጭ እየገባ
የቆየውን ስኳር እንዲቋረጥ በማድረጉና። አገር ውስጥ ያሉ ፋብሪካዎች የህዝቡን ፍላጎት ሟሟላት ይቅርና ከፊሉን ማዳረስ ስለተሳናቸው።
በአጠቃላይ ህዝቡ በተለይ ደግሞ በስኳር ውጤቶች ላይ ተንተርሰው ሲሰሩ የቆዩ በርከት ያሉ ድርጅቶች ስራቸውን እንዳቋረጡና። በነዚህ
ውስጥ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ ወገኖች። በከባድ የኑሮ ችግር ወደቀው እንዳሉ ታውቀዋል፣
ይህ በንዲህ እንዳለ በከተማው ውስጥ ያሉ የህወሓት ኢህአዴግ ካድሬዎች።
ይህን በበላይ ባልስልጣናት እየተፈፀመ ያለው ብልሹ አሰራር ለመቃወም በሚል ምክንያት። ተማሪዎች አሰባስበው ሰላማዊ ሰልፍ ቢያካሂዱም።
የሁመራ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ግን ሃቅነት የሌለው የማስመሰል ተግባር ነው ሲሉ መናገራቸውን ምንጮጫችን ከቦታው አክለው ኣስረድተዋል፣