Friday, December 20, 2013

ማይ ካድራ በተባለው ከተማ አቃቤ ህግ ባለመኖሩ። ፍትህ ለማግኘት እየተንገላታን ነው በማለት ነዋሪዎቹ ምሬታቸው አሰሙ፣



በምእራባዊ ትግራይ ዞን ማይ ካድራ ከተማና አካባቢው የሚገኝ  ፍትህ የሚፈልግ ህብረተሰብ። ወደ አቃቤ ህግ የተለያዩ አቤቱታዎችና ክሶች ይዞ በሚሄድበት ግዜ። ለዚሁ አቤቱታ የሚሰማ በአቃቤ ህጉ ጽሕፈት ቤት የተመደበ ባለ ሞያ ባለመኖሩ። በአካባቢው ወደ ሚገኘው ፖሊስ ጣብያ ቢሄዱም ለኛ የሚመለከት አይደለም ብሎው ስለ ሚመልሱዋቸው። ሁመራ ከተማ ውስጥ ወደ ሚገኘው የቃፍታ ሁመራ አቃቤ ህግ ጽሕፈት ቤት ቢመላለሱም ተገቢ አገልግሎት ስለ ማይጠብቃቸው። ነዋሪዎቹ ላልተፈለገ የግዜ ብክነትና ለተጨማሪ  የገንዘብ ወጪ እንደተጋለጡ። ምንጮጫችን ከሰጡት መረጃ ለመረዳት ተችለዋል፣
    በሌላ በኩል በከተማው ውስጥ አጋጥሞ ያለው የንፁህ ውሃ መጠጥ እጥረት ረጅም ግዜ በማስቆጠሩ። ህብረተሰቡ እለታዊ ምግቡን ለማዘጋጀትና ለመጠጥ የሚሆን ውሃ ተቸግረው። ጥራቱ ካልተጠበቀ ውሃ መጠቀም ግድ ስለ ሆነባቸው። ላልተፈለገ ውሃ ወለድ በሽታዎች መጋለጣቸውና። ችግሩን ለመፍታት በሚል ምክንያት አቤቱታቸውን ለሚመለከታቸው የዞንና የወረዳ ባለስልጣናት ቢያቀርቡም። ሰሚ አካል ሊያገኙ እንዳልቻሉ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣