በመረጃው መሰረት በምዕራብ ጎጃም ዞን
ከሚገኙ 13 የገጠር ወረዳዎችና 2ት የከተማ አስተዳደሮች፤ ጠቅላላ በስድስት ወር ውስጥ በጤና ዙርያ ያለውን የስራ
አፈፃፀምና ግምገማ ምን እንደሚመስል በቡሬ ከተማ ከጥር 13 እስከ 16 /2006 ዓ.ም በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የተመራ ሲሆን። በተካሄደው
ስብሰባም ተሳታፊዎቹ ብዙ ነገሮችን እንዳስነሱ የገለፀው ይህ መረጃ። በተለይ ደግሞ የዞኑ ማህበረሰብ ሳያምንበትና ሳይወያይበት ተግባራዊ
እንዲሆን የተደረገው ይህ የጤና መድህን ቅድመ ክፍያ የሚል አሰራር። ህዝቡ እንዳልተቀበለውና በመቃወም ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችልዋል፣
መረጃው ጨምሮ እንደሚያስረዳው መላው
የዞኑ ህብረተሰብ በተለይ ደግሞ አብዛኛውን ስፍራ የሚይዘው የገበሬው ማህበረሰብ ለመለስ ፋውንዴሽና ለአባይ ግድብ እየተባለ የምናዋጣው
ገንዘብ ሳይበቃ። አሁን ደግሞ አገልግሎቱ ለማይታወቅና ላልተወያየንበት በፍፁም አንከፍልም የሚል አቋም ይዞ ስለሚገኝ። ይህም በአብዛኛው
ህዝብ ተቀባይነት ያጣ ሓሳብ ስለሆነ። በአስተዳድሩ በኩል ትልቅ ችግር ፈጥርዋል ሲሉ የስብሰባው ተካፋዮች ላነሱት አጀንዳ። ስብሰባውን
ይመሩት የነበሩ ሓላፊዎች ለመድረኩ መቋጫ ሳያደርጉለት አድበስብሰው በማለፋቸው ምክንያት በህዝቡና በአስተዳደሩ መካከል የከፋ አለመግባባት
ተፈጥሮ እንደሚገኝ ገልፀዋል፣