በመረጃው መሰረት በፍኖተ ሰላም ከተማ በተለያዩ ጽሕፈት ቤቶች የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች። ባልፈጸሙበት
ወንጀል ስርዓቱ ባቋቋመው የጸረ ሙሱና ኮሚሽን ውስጥ የሚሰሩ የበላይ አስተዳዳሪዎች እየተሰቃዩ በመሆናቸውና። ከስራ ገበታቸው እንዲለቁ
እየተገደዱ ነው ሲል መረጃው አስታውቀዋል፣
በሰራተኞቹ ላይ የተለያየ ወንጀል እየፈጸሙ
ከሚገኙ አስተዳዳሪዎች ውስጥ። የዞኑ ከንቲባ አቶ አሸበር ዮሃንስና ሌሎች ባለስልጣኖች መሆናቸው የጠቆመዉ መረጃው። በዚህ ምክንያትም
በከተማው ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች። በከባድ ስጋት
ላይ ወድቀው እንደሚገኙ ያገኘነው መረጃ አመልከተ፣
በተመሳሳይ መንገድ በምዕራባዊ ዞን ወንበርማ
ወረዳ። ኮሊ፤ ጭራር፤ ጋለቤድና፤ ወይንማ ቀበሌዎች የሚገኙ ሊቀ
መንበሮች። ለግብር፤ ለጤና ጣብያና ስፖርት ተብሎ ከህዝብ የተውጣጣ ገንዘብ። በግዜው ለመንግስት ገቢ ሊያድርጉት ባለ መቻላቸው ታስረው
እንደሚገኙ ቢታወቅም። ነገ ከሃላፊዎች ባላቸው ግንኝነትና። በጉቦ በሚንቀሳቀስ ፍርድ ቤት ምክንያት። ነጻ የሚለቀቁ መሆናቸው። የአካባቢው
ነዋሪ ህዝብ በመግለፅ ላይ እንዳለ የደረሰን መረጃ ኣስታወቀ፣
ከዞኑ ሳንወጣ በጃዊ ወረዳ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች
የአገር እና የህዝብ ገንዘብ እያጠፋፉ እንደሚገኙ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ኣስታወቀ፣
በአማራ ክልል ጃዊ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ
የህወሃት ኢህአዴግ አስተዳዳሪዎች የአገርና የህዝብ ገንዘብ በማጠፋፋት ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ የጠቆመው መረጃው። ገንዘብ
በማጠፋፋት ስራ ከተሰማሩት ውስጥ አቶ ገበየሁ የተባለ ቀደም ሲል የወረዳዋ ምክትል አስተዳዳሪ የነበረና በሃላ ዋና አስተዳዳሪ ሁኖ
እንዲሰራ በከፍተኛ ባለስልጣኖች የተሾመው ይህው አስተዳዳሪ። ብሃሳብና በአስተያየት ድጋፍ ላደረጉለት 4 ሰዎች ለየእንዳንዳቸው
30 ሺ ብር ተገቢነት በሌለው መንገድ ገንዘብ እንዲከፈላቸው እንዳደረገ የደረሰን መረጃ አመለከተ፣
የተገኘው መረጃ ጨምሮ በወረዳዋ የሚገኙ
አስተዳዳሪዎች ከዋና አስተዳዳሪ ጀምሮ እስከ ቀበሌ አስተዳደር በዚሁ ተገባር ተሳስረው እንደሚገኙ ገልጾ። በተለይ ፍልፍል በተባለው
ቀበሌ ውስጥ ሲመራ የነበረ አቶ ገበዮህ የተባለ ሊቀ መንበር ከግብር የተሰበሰበ ከ 34 ሺ ብር በላይ ሰርቆ ከአካባቢው እንደተሰወረ
የደረሰን መረጃው አስረድተዋል፣