Friday, April 18, 2014

በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ከ500 በላይ መኖሪያ ቤቶች እንዲፈርሱ የሰሜን ጎንደር ማዘጋጃ ቤት ሃላፊ ትዕዛዝ አስተላለፈ።



በመረጃው መሰረት- በጎንደር ከተማ በተለምዶ ጨረቃ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በህጋዊ መንገድ ከ6 ዓመት በፊት የተሰሩ ከ500 በላይ መኖሪያ ቤቶች እንዲፈርሱ የጎንደር ከተማ ማዘጋጃ ቤትና የከተማዋ ምክር ቤት ሃላፊዎች በአንድ ላይ ትዕዛዝ እንዳስተላለፉ ምንጮቻችን ከስፍራው አስታወቁ።
     የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ በተለይ ደግሞ የችግሩ ሰለባ  የሆኑ ዜጎች ትክክለኛ ከሆናችሁ እየገነባን በነበረንበት ሰዓት ለምን ዝም አላችሁ የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ደማችን ይፈሳል እንጂ ቤታችንን አታፈርሱም በማለት ሃይለኛ ተቃውሞ እያስነሱ መሆናቸውም መረጃው አክሎ አስረድተዋል።