Friday, April 18, 2014

በቤንሻንጉል ክልል የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሄር ተወላጆች ከቀያቸው በሃይል ተገድደው እየተፈናቀሉ መሆናቸውን ከአካባቢው የተገኘው መረጃ ገለጠ።



እነኚህ 4.500 ሺ የሚሆኑ አብዛኞቹ ኢንቨስቶሮች የሚገኙባቸው የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑ አርሶ አደር ወገኖቻችን በሃገራቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥሮው በወያኔ ኢ,ህ.አ.ደ.ግ ስርአት ካድሬዎች ከቀያቸው እየተፈናቀሉ  መሆናቸውን የገለፀው መረጃው በርከት ላሉ አመታት ሲኖሩ ከቆዩበት ባምባስ፤ ሶጌና አሶሳ ከተባሉ ወረዳዎች በሃይል እየተፈናቀሉ መሆናቸው ተገለፀ።
    እየተፈናቀሉ ያሉት ዜጎቻችን በላያቸው ላይ እየወረደ ያለው ግፍ መፍትሄ እንዲደረግለት በማለት ወደ ሚመለከታቸው አካላት እሮራቸውን እንዳቀረቡና ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ያደርጉለታል ከተባሉት የበላይ ባለስልጣኖች ውስጥ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የብአዴን ፅሕፈት ቤት ሓላፊ የሆነው  አቶ አላምነው መኮነን እንዲሁም 3 የክልሉ ባለስልጣናት  ስለ ጉዳዩ አስመልክተው ተፈናቃዮቹ በቦታቸው እንዲቆዩ የሚል ሃሳብ አስነስተው ባደረጉት ንግግር ሁሉም ባለስልጣናት ሊስማሙ እንዳልቻሉ ምንጮቻችን በላኩት መረጃ ለማወቅ ተችልዋል።
    በመጨረሻም የባምባስ ወረዳ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ብዛት ያላቸውን የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርአት ታጣቂዎች በማሰማራት ጭካኔ በተሞላበት መንገድ  ዜጎቹ ከሚኖሩበት  ጀቢ፤ ጠህናና፤ ደንበጫ፤ ሰከላ፤ ቋሪት፤ ደጋ ዳሞት፤ ቡሬ አዴታና በሌሎችም ስፍራዎች ላይ 4.500 ሺ የሚደርሱ ዜጎቻችንን በሃይል አስገድደው እንደ-አፈናቀሏቸው መረጃው አክሎ አስረድተዋል።