እነዚህ በቃፍታ ሁመራ ወረዳ፤ አደባይ ጣብያ በእርሻ ስራ ላይ ሲተዳደሩ የቆዩ ከ62 በላይ የሚሆኑ ገበሬዎች
በህጋዊ መንገድ ከተሰጣቸው በኋላ ጉልበታቸውን አፍስሰው ለእርሻ ያዘጋጅትን መሬታቸውን በቀበሌው አስተዳዳሪዎች በመነጠቃቸው ምክንያት
ለከባድ ችግር እንደተጋለጡ ተገለፀ፣፣
መረጃው በማስከተል ተበዳዮቹ በላያቸው
ላይ የደረሰውን በደል መፍትሄ እንዲደረግላቸው ወደ ወረዳ ሄደው ብሶታቸው ቢያቀርቡም የምናውቀው ነገር የለም በቀበልያችሁ ሄዳችሁ
ፍቱት የሚል መልስ እንደተሰጣቸውና፣ አሁንም ተስፋ ሳይቆርጡ ወደ ዞን በመሄድ ያቀረቡት አቤቱታም ወጤት እንዳላገኙበት ለማወቅ ተችለዋል፣፣
ይህ በደን ሽፋን ያለምንም ተለዋጭ መሬት ይዞታቸውን የተነጠቁት ወገኖች የሚያርሱትን
መሬት በማጣታቸው ምክንያት በተለይ ለቀጣይ አመት እስከነቤተሰቦቻቸው ችግር ላይ እንዳይወደቁ ትልቅ ስጋት እንደተጋረጠባቸው መረጃው
አክሎ አስረድተዋል፣፣