Tuesday, July 15, 2014

በቃፍታ ሁመራ ወረዳ በተበላሸ የህወሃት ኢ.ህ.አ,.ዴግ የመሬት አስተዳደር ስርዓት የተነሳ በሚቀሰቀሱ ጥላቻዎች በርካታ ዜጎች አካላቸው እየተጎዱና ህይወታቸውም እያጡ መሆኑን ምንጮቻችን ከስፍራው ገለፁ፣፣



ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለጹት ሰኔ 26/ 2006 ዓ.ም በቃፍታ   ሁመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ በዋል በተባለ የእርሻ ቦታ ጥራት በጎደለው የመሬት ሽግሽግ አንድ ፀጋይ ገብረ መስቀል የተባለ ግለሰብ ከጌታቸው ታፈረና ሰለሞን ሃፍተ ከተባሉ ነዋሪዎች መሬት ተቀንሶ የተሰጠውን መሬት ሊያርስ በሄደበት ጊዜ  የቀድሞው የመሬቱ ባለቤቶች የማንን መሬት ልታርስ መጣህ በማለት በዱላና በፋስ አካሉን ቖራርጠው ጥለውት እንደሄዱ  ታውቋዋል፣፣
   ይህ ሞቷል ብለው በረሃ ጥለውት የሄዱት ተደብዳቢ ፀጋይ ገብረ መስቀል የተባለ ወገን ሌሎች ሰዎች ሲንቀሳቀሱ በህይወት እንዳለ ሲያቁ ወደ ህክምና የወሰዱት ሲሆን ለተፈፀመው ይሁን ሲፈፀም ለቆየው ጥላቻና የህይወት መጥፋት መነሻው የስርዓቱ ካድሬዎች እየተከተሉት ባለው ፍትሃዊነት የጎደለው የመሬት አስተዳደር ምክንያት በህዝብ መካከል ግርግር እንዲፈጠር በማድረግ የስልጣን እድሜያቸውን ለማስረዘም የሚያደርጉት ሴራ መሆኑን በርካታ ነዋሪዎች እየገለጹ እንዳሉ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣፣