Tuesday, July 8, 2014

ድርጅታዊ መግለጫ! በየመን መንግስትና በወያኔ ስርአት በግንቦት 7ዋና ፀሃፊ ታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌ የተወሰደውን ያፈና ተግባር በመቃወም ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ።



የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት ባለፉት 23 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል እየፈፀመ መቆየቱና አሁንም እየቀጠለበት መሆኑ ይታወቃል የወያኔ አምባገነን ስርአት ህዝቡን እየጨፈጨፈና ለነፃነት የቆሙትን ቁርጠኛ ታጋዮች በመግደል፣ የህዝቡን የትግል ማእበል መግታት እንደማይቻል ካለፉት አባቶቹ መማር በተገባው ነበር።
  ትናንት በወያኔዎች ቀጥተኛ መሪነት ይካሄድ በነበረውና በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ጀግኖች ለጭቁኑ ህዝብ ሲሉ በጠላት ስር የወደቁና ባውደ ውጊያ ፊት ለፊት ተዋግተው መስዋእትነት በመክፈላቸው፣ ህዝባዊ ትግሉ በበለጠ እልህና ቆራጥነት ሲቀጥል እንጂ፣ በከፈለው መስዋእትነት ተደናግጦና ተስፋ ቆርጦ ትግሉ ወደ ኋላ ሲመለስና ትርጉም የለሽ ሲሆን አልታየም።
   ምክንያቱም ትግል ሲባል ሁሉም አይነት መስዋእትነት ከፍለህ ከአፈናና  ከጭቆና ነፃ በማውጣት ለህዝቡ ፍትህ፤ እኩልነትና ዴሞክራሲ ማስፈን ስለሆነ፣ ይህ በታጋይ እንዳርጋቸው ፅጌ ያጋጠመው ድርጊትም ለዘአለም ህያው ነው።
    ስለሆነም የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ት.ህ.ዴን/ ይህ በየመን መንግስት በታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌ ላይ የተፈፀመው ታሪካዊ ስህተት በሁሉም የኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች ላይ የተፈፀመ እንደሆነ በማመን እኩይ ተግባሩን በፅኑ እናወግዘዋለን።
    ይህ የታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌ ለህዝብ ብሎ የከፈለው መስዋእትነት ደግሞ። ያለፉት ጀግኖች አላማቸውን አምነው ለህዝብና ለሃገር ብለው እየከፈሉት የመጡትን ከባድ የመስዋእትነት ዋጋ  በመከተል ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የአንዳርጋቸው ፅጌና የሚሊዮኖች ታጋዮች ዋጋ የከፈሉለት ትግል ወደ ድል ለማብቃት ትግሉ እንዲጠናከርና የአምባገነኑ ስርአት እድሜ እንዲያጥር በዚህ አጋጣሚ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ት.ህ.ዴ.ን / ጥሪውን ያቀርባል።
                   ዘለአለማዊ ታሪክ እንጂ ዘለአለማዊ ህይወት የለም!
                             የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
                                   ሓምሌ 2/2006 ዓ/ም
  ድል ለጭቁኖ!!