Thursday, July 24, 2014

በሁመራ ከተማ ሐምሌ 4/2006 ዓ.ም በተከሄደው የሴቶች ኮንፈረንስ ላይ ህወሃት ኢህአዴግ የትግላችንን ፍሬ አላካፈለንም በማለት በነበረው መድረክ ጠንካራ ክርክር እንዳደረጉ ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ።



በሁመራ ከተማ የተካሄደው የሴቶች ኮንፈረንስ የህወሃት ኢህአዴግ ባለስልጣኖች የሃገራችንን ሴቶች በሁሉም የስራ መስክ ያላቸው ተሳትፎ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንዳለ አስመስለው የገለፁ ቢሆኑም በስብሰባው ላይ የተሳተፉ ሴቶችም በበኩላቸው እኛ ስርዓቱ እንደሚለው ሳይሆን በንግድ ስራ እንኳን ተሰማርተን መብላት አልቻልነም ከአቅማችን በላይ ግብር እየተጠየቅን ትርፋችን ድካምና ኪሳራ ካልሆነ በስተቀር ያገኘነው ምንም አይነት ጥቅም የለም በማለት ስርዓቱ ይዞት በቀረበው አጀንዳና  እነሱን በማይገልጸው ሪፖርት እጅግ በጣም እንደተናደዱ ለማወቅ ተችሏል።
     በነበረው ስብሰባ ላይ ሃሳባቸውን በግልፅ ካቀረቡ ሴቶች ለመጥቀስ ማሚት አታላይ የምግብ ቤት ባለቤት የነበረች፤ መሰረት አሸናፊ የግሮሰሪ ባለቤት የነበረችና ሌሎችም ሲሆኑ እነዚህ ሴቶች  እንደገለፁትም በተለያዩ የውጊያ አውድማዎች ከወንድሞቻችን ጋር በመሆን እኩል ተዋግተናል በሃገራዊ ልማትም ቢሆን እየተሳተፍን ስንገኝ የተጠቀምነው ነገር ግን የለም እናንተ ግን የተጠቀምን አስመስላችሁ በመገናኛ ብዙሃን እያቀረባችሁት ያለው ሃሳብ  እኛን በፍፁ የሚገልፅ አይደለም በማለት የስርዓቱን የውሸት አጀንዳ እንደተቃዎሙት የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።