Tuesday, July 15, 2014

በአድዋ አካባቢ ተዘርቶ የበቀለውን ሰብል በተምች እየተበላ በባለሙያ የተደረገ አስቸኳይ እርዳታ ባለመኖሩ አርሶ አደሮች ምሬታቸውን እየገለፁ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው አስታውቀዋል፣፣



    በትግራይ ማዕከላዊ ዞን የአድዋ ገጠር ወርዳ  በእርሻ ስራ የሚተዳደሩ አርሶ አደሮች የክረምት ወቅት ጠብቀው የዘሩት ሰብል በተምች በተባለ ፀረ ሰብል  ትል  እየበላው ባለበት ወቅት አስቸኳይ እርዳታ እንዲደረግላቸው ሰኔ 29 /2006 ዓ/ም ወደ ሚመለከተው አካል ጠይቀው የሚረዳ ባለሙያ ባለማግኘታቸው ሃላፊነት በማይሰማው አስተዳዳሪ ላይ ምሬታቸውን እያሰሙ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፣፣
    ምንጮቻችን ጨምረው እንደገለፁት አርሶ አደሮች የሚያረካ ምርት እንዲያፍሱለት ይጠብቁት የነበረው ቡቃያ በዚህ ትል ከመበላቱ በፊት አንዳንድ ምልክቶች እንደነበሩና ፀረ ተባይ መድሃኒት እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ጠይቀው አወንታዊ ምላሽ ሳያገኙ በመበላቱ “ልጆቻችንን ምን ልናበላቸው ነው ፥ይህስ በአስገዳጅ ውሰዱ እየተባለ በብድር የወሰድነው  ማዳበሪያና ምርጥ ዘርስ ከምን አምጥተን ልንከፍለው ነው በማለት በስርዓቱ ላይ የተሰማቸውን ቅሬታ እየገለፁ እንደሆኑ ታውቋል፣፣
 ምሬታቸውን እየገለፁ ከሚገኙ ወገኖችም የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል ብርሃነ ነጋሽ፥ ገብረዝጊሄር መዓሾና ቀሺ ወሉ ግርማይ የተባሉት የሚገኙበት ሲሆን እነሱም “ በመንግስት ባለስልጣን በየስብሰባውና በየሚዲያው እርሻ የመጀመሪያ ትኩረታቸው እንደሆነ የሚናገሩት ለፖለቲካዊ ሸቀጥ እንጂ ለተግባራዊነቱስ በፍፁም የሉም  ከነበሩ ከዚህ የበለጠ ወራሪ የለም  በሰዓቱ ሊያግዙን ይገባ ነበር” ሲሉ መናገራቸውን የተገኘው መረጃ ጠቅሷል፣፣