Friday, July 18, 2014

በመኾኒ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች የእርሻ መሬታቸውን በዞኑ አስተዳዳሪዎች እየተቀሙ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው ገለፁ፣፣



በመረጃው መሰረት በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን መኾኒ ወረዳ  የገርጀለና የ“ቶ” ቀበሌ አርሶ አደሮች የሚጠቀሙበትን ሰፊ የእርሻ መሬት በዞኑ ባለስልጣናት የተላኩ ካድሬዎች መኖሪያ ቤታቸውን እያፈረሱ በመቀማት ሽርክና ለፈጠሩላቸው ኢንቨስተሮች እየሰጡ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፣፣
   በዚህ ተግባር የተቆጡ የአካባቢው ነዋሪዎች ተለዋጭ መሬት ወይም ካሳ ሳይኖረው ህጋዊ መሬታቸን ለምን እንቀማለን የሚል አቤቱታ ለሚመለከተው አካል አቅርበው አዎንታዊ ምላሽ የሚሰጣቸው ስላጡ በአካባቢው ተቃውሞ እንደተቀሰቀሰ ታውቋል፣፣
   ከወረዳው ሳንወጣ ከስደት ለተመለሱ ዜጎች ተብሎ በፌደራል መንግስት የተመደበ 48 ሚሊዮን ብር እስካሁን ከስደት ለተመለሱት ዜጎች በገንዘቡ የተደረገላችው ምንም ነገር ባለመኖሩና የተገባላቸው ቃል ባለመተግበሩ ምክንያት ለሁለተኛ ጊዜ ለስደት እየተዳረጉ መሆናቸውን መረጃው አመልክቷል፣፣