Friday, July 18, 2014

በትግራይ ደቡባዊ ዞን መኾኒ ከተማ የአረና ተቃዋሚ ድርጅት በጠራው “ዘመቻ አብረሃ ደስታ ለፍትህና ለነፃነት” በሚል ስያሜ ሃምሌ 6/ 2006 ዓ/ም ስብሰባ እንደተካሄደ ተገለፀ፣፣



በመረጃው መሰረት የስብሰባው አላማ በወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የደህንነት አባላት በፖለቲካ ልዩነቱ ምክንያት በአዲስ አበባ ታስሮ የሚገኘው የመቐለ ዩንቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር የሆነው አብረሃ ደስታ እንዲፈታ የሚጠይቅ እንደሆነ መረጃው ገልፆ ይህ ስብሰባ እንዳይካሄድ በጥብቅ ሲከታተሉት የቆዩ የስርዓቱ ካድሬዎች እንዲደናቀፍ እንዳደረጉ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣፣
    የተጠራውን ስብሰባ ለማደናቀፍ የተንቀሳቀሱ የስርዓቱ ተላላኪ አስተዳዳሪዎች ከደቡባዊ ዞን አስተዳዳሪ መምህር ሃፍቱ ኪሮስ የተላኩ የፖሊስ አባላትና ደህንነቶች በመኪናና በሞተር ሳይክል እየተንቀሳቀሱ  ለነዚህ ፍትሕ ይንገስ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ያሉት ወገኖች  ፀረ ልማትና  አሸባሪ የሚል ስም እየሰጡ እንደበተኗቸው ታውቋል፣፣
    በመጨረሻም የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የፀጥታ አባላት የፖለቲከኛ አብረሃ ደስታን መኖሪያ ቤትና ፅህፈት ቤቱን ፈትሸው ያገኙትን ንብረት በመኪና ጭነው እንደወሰዱት ለማወቅ ተችሏል፣፣