Friday, July 25, 2014

በቤንሻጉል ጉሙዝና በኦሮምያ መካከል በምትገኘው በቱንጉ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች የኦነግ አባላትና ደጋፊዎች ናችሁ እየተባሉ በወያኔ ኢህአዴግ ስርአት ግፍ እየወረደባቸው መሆኑን ምንጮች ከቦታው ገለፁ።



እነዚህ በቤንሻንጉል ጉምዝና በኦሮምያ ቱንጉ በተባለው አካባቢ የሚገኙ ንፁሃን ወገኖች የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት የኦነግ አባላት ናችሁ በማለት ግፍ እያወረዱባቸው መሆኑንና በዚህ ሳምንት ብቻ ሶስት ንፁሃን ዜጎች ለግዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለው እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው በማስከተል ከተገደሉት አንዱ በንግድ ስራ ሲተዳደደር የነበረ ወገን ሲሆን የቀሩት ሁለቱ ደግሞ የስርአቱ ተላላኪዎች መሆናቸው፤  በተወለዱበት ቦታ በስርአቱ ካድሬዎች በሰላም መኖር ያልቻሉ ዜጎቻችን  በላያቸው ላይ እየወረደ ያለው አሰቃቂ ግፍ እንዲቆም በማለት ለሚመለከታቸው አካላት ያቀረቡትን ጥያቄም መፍትሄ የሚሰጥ ወገን ባለማግኘታቸው ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል።