በምንጮቻችን መረጃ መሰረት-
በስልጣን ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ ገዢ መደብ በመጭው 2007 ዓ,ም አካሄደዋሎህ ለሚለው የይስሙላ ምርጫ እንቅፋት ይሆኑኛል ለሚላቸው
በሰላማዊ መንገድ ለሚታገሉ ድርጅቶች፤ አመራሮችንና አባሎችን አሸባሪዎች ናቸው እያለ በሃሰት እየወነጀላቸው ሲሆን በዚህ የሃሰት
ወንጀ ከተወንጀሉት ውስጥ።
·
አቶ አየለ የተባለ በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ-ዳሞት
ወረዳ የሚኖር ከዚህ በፊት ከቅንጅት ድርጅት ጋር በመሆን ህዝብ ሲያስተባበር
የነበረ፤
·
አቶ ጥላሁን የተባለ በሰሜን ጎንደር ዞን የመኢአድ
ዋና ፀሃፊ የነበረውንና ሌሎችንም ስማቸው የልተገለፀ ንፁሃን ዜጎች ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት አላቸው በማለት አስሯቸው እንደሚገኝ
ምንጮቻችን አስታወቁ።
እንደዚህ አይነት ፀረ ህዝብ አካሄድ የኢህአዴግ ገዢው መደብ መለያ ባህሪው
እንደሆነና በአሁኑ ጊዜ ይህንን እኩይ ተግባሩን በመላው የሃገራችን አካባቢዎች ታይቶ በማይታወቅ መንገድ አጠናክሮ እየቀጠለበት እንደሚገኝ
ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ ለመረዳት ተችሏል።