በመረጃው መሰረት በአማራ
ክልል ወደ ኋላ በቀሩት ወረዳዎች ተመድበው የሚሰሩና የአቅም ጉድለት አለባቸው የተባሉ የብአዴን ካድሬዎች የአቅም ማሳደጊያ በሚል
ሰበብ በከፍተኛ የድርጅቱ አመራሮች እየተሰጠ ያለው ስልጠና እስከ መስከረም 1/2007 ዓ.ም እንደሚቀጥል የገለፀው ይህ መረጃ በሚካሄደው
ስልጠናም ከነፍስ ወከፍ ወረዳ አምስት አምስት ካድሬዎች ተመልምለው ባህርዳር ከተማ እንደገቡ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ጨምሮ
እንደሚያስረዳው እነዚህ በድብቅ ጥሪ የተደረገላቸው የወረዳዎቹ አመራሮች ዋና መሰብሰቢያ አጀንዳቸው በ2007 ዓ,ም ለሚካሄደው ምርጫ
ግንባር ቀደም ሆነው የተሰጣቸውን ግዴታ እንዲተገብሩ፤ ህዝቡን እንዲያስተባብሩ እየተደረገ ያለ የሚስጥር ስብሰባ እንደሆነና። ለዚህ
ሚስጥራዊ ስብሰባ እንዲሳተፉ ጥሪ ከተደረገላቸው ወረዳዎች የተወሰኑትን ለመጥቀስ- ከአዊ ዞን 3ት፤ ከኦሮሚያ ልዩ
ዞን ከከምሴ ደግሞ 2ት፤ በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አክሎ አስርድቷል።