ምንጮቻችን በሰጡት መረጃ መሰረት ከነሃሴ 18 እስከ 20/2006 ዓ/ም
ከሸርቆሌ ጀምሮ ህዳሴ ግድብ እየተሰራበት እስካለው ቦታ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በከፈቱት ቶክስ ምክንያት ወደ ህዳሴ ግድብ
ሰራዊትና መሳርያዎች እየተጓጓዘ መሆኑን የገለፀው መረጃው ነሃሴ 25/2006 ዓ/ም ከ20 በላይ ወታደራዊ ኦራል ተሽከርካሪዎች የተለያዩ
መሳርያዎች ጭነው እንደገቡ ታውቋል።
በቦታው በቀን ስራ ላይ ተሰማርተው እየሰሩ የነበሩት ሰራተኞች ቦታውን ትተው
መውጣታቸውና ስራውም ለግዜው መቓረጡን ባካባቢው ከተሰማሩት የሰራዊቱ አካላት በደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏዋል።
ከኽልሉ ሳንወጣ በከማሽ ዞን ሶጌ ወረዳ የሚገኙ የገዢው ድርጅት አባላት
ከህዝባቸው ጋር ሆነው የራሳቸውን ባንዴራ በማዘጋጀትና ልዩ ፌስቲቫል በማድረግ ከክልላቸው ተወላጅ ውጭ የሆኑትን የኦሮሞና የአማራ
ተወላጆች አያስተዳድርኑም ብለው ቃለ መሃላ በመፈጸም ለኦሮሞ ሽናሻ ብሄረሰብ ከወረዳው እንዳወጥዋቸው ለማወቅ ተችለዋል።
መረጃው ጨምሮ እንደገለፀው ይህ ተግባር ያገራችንን ምስል አሳጥቶ የሚበታትንና
የኢህአዴግ መንግስት የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ብሎ ራሱ እየፈፀመው ያለ እኩይ ተግባር እንደሆነና ህዝቡ ምሬቱን እየገለፀ መሆኑን
የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።