ይህ አስገዳጅ ስብሰባ በወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች እየተመራ መሆኑን
የገለፁት ምንጮቻችን በተለይ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በካድሬዎች ተደጋግሞ የተተረከላቸውን የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የዲሞክራሲ ስርዓት
ግንባታ በሚለው ርዕስ ስር ተማሪዎች በርካታ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን የመድረኩ መሪዎች መልስ መስጠት ባለመቻላቸው ከ40 በላይ የሚሆኑ
ተማሪዎች መድረኩን ረግጠው መውጣቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል በመተማ ወረዳ ልዩ
ስሙ ግጨው ስለተባለው መሬት ጉዳይ የሚመለከት? በክልሎች ዙሪያ ያለው የመሬት አከላለል በሚመለከት፤ በአሁኑ ሰዓት በኦሮሚያ ክልል
የምኒልክ ሃውልት መገንባት ለምን አስፈለገ? እንዲሁም የቅማንት ብሄረሰብ በዞናቸው ሊጠሩ ይገባል የሚሉና ሌሎችም እንደሚገኙበት
ምንጮች አስረድተዋል።
በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች በበኩላቸው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ
የ23 ዓመት የመሰረተ ልማት ግንባታ በጣም ዝቅተኛ ነው በማለታቸው የድርጅቱ ባለስልጣኖች ስለሰጉ ተማሪዎችን ለመቀስቀስ ሲባል ሁሉም
በአዲስ ኣበባ የሚገኙ የህዝብ መጓጓዣ አገልግሎት የሚሰጡ አውቶቢሶች ተማሪዎቹን ለመጎብኘት በመታዘዛቸው ኗሪው ህዝብ በትራንስፖርት
እጥረት ተቸግሮ እንደዋለ ታውቋል።
ይህ በእንዲህ
እንዳለ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ለ2007 ዓ/ም ለሚካሄደው ምርጫ ደጋፊ እንዲያገኝ
ተማሪዎችን ለማሳመን ያደረገው ጉብኝት ሊሳካለት እንዳልቻለ መረጃው ከገለፀ በኋላ ተማሪዎች ያዩት የሚያቁትን መንገድና የጋራ መኖሪያ
ቤት አዲሳቸው አለመሆኑን በግልና በቡድን እየተነጋገሩበት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።