Friday, September 26, 2014

በሃገራችን ኢትዮጵያ የሚገኙ በቀድሞ ስራዊት ያገለገሉ ወገኖቻችን ከተቓዋሚ ድርጅቶች ጋር ግንኝነት አላችሁ በሚል ምክንያት ግብረ ሃይል በሚል በተቛቖሙት ሃይሎች ታድነው እየታሰሩ መሆናቸው ተገልጸ።



    ቀደም ሲል በስርአቱ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ሆነው ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ በተለያዩ ምክንያት ከውትድር ስራ ወጥተው ወደ ግል ኑፘቸውን የገቡ ንጹሃን ዜጎቻችን በገዢው ስርአት በተደራጁ ግብረ ሃይል ታድነው እየታሰሩ መሆናቸው የገለጸው መረጃው የታሰሩበት ምክንያትም በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ በትጥቅ ትግልና በፖለቲካው መስክ እያካሄዱ ካሉት ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ግንኝነት አላችሁ በሚል ጥርጣሬ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
     መረጃው በማስከተል የኢህአደግ ስርአት ባለ-ስልጣናት በህዝቡ ላይ ያላቸው ተቀባይነት በሚያስገርም ሁኔታ በማሽቆልቆሉ ምክንያት 2007 ዓ/ም በሚካሄደው የይስሙላ መርጫ ላይ ሊያደናቅፉን ይችላሉ የሚልዋቸው የቀድሞ ወተሃደሮችን ያለ ምንም ተጨባጭ ምክንያት እያሰርዋቸው እንደሚገኙና እስካሁንም በአዲስ አበባ ብቻ ከ120 በላይ የሚሆኑ ንፁሃን ዜጎች ታጠቕ በሚባለው እሰር ቤት ካለ ምንም ወንጀል አጉሮው እያሰቃይዋቸው እንዳሉ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።