Monday, October 13, 2014

በአዲስ አበባ ከተማ መስከረም 24/2007 ዓ.ም የዱቄት ፋብሪካ ለመትከል የመሰረት ድንጋይ በሚቀመጥበት ሰዓት የፋብሪካው ስም በጠቅላይ ሚንስትሩ ባለቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋይ ሊሰየም ነው ስለተባለ የከተማው ህዝብ ጠንካራ ተቃውሞ እንዳስነሳ ምንጮቻችን አስታውቁ፣

www.demhit online.com




ምንጮቻችን ከከተማዋ የላኩልን መረጃ እንደሚያመለክተው በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ለገጣፎ ተብሎ በሚጠራው 60 ሄክታር በሚሆን መሬት ላይ የሚያርፈው የዱቄት ፋብሪካ፤ በጠቅላይ ሚኒስተሩ ባለቤት  ወ/ሮ ሮማን ተስፋይ ስም እንዲጠራ በተወሰነበት ጊዜ፤ ይህንን ድርጊት የሰማው ህብረተሰብ ጠንካራ ተቃውሞ እንዳደረገ ለመወቅ ተችሏል፣
  መረጃው ጨምሮም ህብረተሰቡ ፋብሪካው የሚሰራው በህዝብ ገንዘብ ነው ለምን? በግለሰብ ደረጃ እንዲጠራ መንግስት የወሰነው በማለት ተቃውሞውን እያሰማ እንደሆነና፤ በሚካሄደው የህዝብ ተቃውሞም ሰማያዊ ፓርቲና ሌሎችም ተቃዋሚ ድርጅቶች ከህዝብ ጎን እንደተሰለፉና ሁኔታውንም አጥብቀው በማውገዝ ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል፣